
Fana Broadcasting Corporate SC
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ከዚህ በታች ለተመለከቱት ክፍት የስራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
▪️1.የስራ መደቡ መጠሪያ፦- ፍሎር ማናጀር
ተፈላጊ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ፡- በኤሌክትሮኒክስ፣ሲኒማቶግራፊ፣ በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣በጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን፣ ቲያትርካል አርት እና ተመሳሳይ መስክ የኮሌጅ ዲፕሎማ እና 4 ዓመት አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ያለው/ያላት ወይም ቢኤ/ቢ.ኤስ.ሲ ዲግሪና 2 ዓመት አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ያለው/ያላት
ደረጃ – Vll ብዛት – 1 /አንድ/
▪️2. የስራ መደቡ መጠሪያ፡- የጋራዥ ባለሙያ
ተፈላጊ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ፡- በአውቶ ሜካኒክስ፣በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ እና በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የኮሌጅ ዲፕሎማ እና 4 ዓመት አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ያለው/ያላት
ደረጃ -Vl ብዛት – 1
የቅጥር ሁኔታ – በቋሚነት
ደመወዝ፡- በድርጅቱ ስኬል መሠረት
የስራ ቦታ:- ዋናው መ/ቤት /አዲስ አበባ/
መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ሲቪ ፣የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃችሁን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ ከየካቲት 20 እስከ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በሰው ሀብት ስራ አመራር ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በመቅረብ ወይም https://fanabc.com/jobs ኦንላይን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አ.ማ.
+251 – 115 -51-67-77
አድራሻ፡- ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ
ማሳሰቢያ፡- ከግል ድርጅት የሚመጡ የስራ ልምዶች የስራ ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡